Love your Neighbor

the Five Pilars

w icon-08

Helping

መርዳት

የተረጂነትና የጥገኝነት አስተሳሰብ ሰዎች ራሳቸውን ለመለወጥ ጥረት እንዳያደርጉ ትልቁ ዕንቅፋት ነው። ይህንን ዕንቅፋት ከመንገድ አስወግዶ በአስከፊ ድህነት ውስጥ የሚኖሩትን ተረጂዎች ወደ አምራችነትና ወደ ረጂነት ለማሻገር ትምህርቶች፣ ሥልጠናዎች እና የመንቀሳቀሻ ድጋፎች ግዙፍ ድርሻ አላቸው። ላቭ ዩር ኔበር በየአካባቢው ያሉ በአስከፊ ድህነት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች አቅማቸውን ያገናዘበ ትምህርትና ሥልጠና እንዲያገኙ እንዲሁም ለሥራ መንቀሳቀሻ ድጋፎች እንዲመቻቹላቸው በትጋት ይሠራል።
All lives are precious! To live a dignified life basic need must be met; food, shelter, and clothing coupled with access to clean water, basic healthcare, and the ability to send children to school are the pillars of a dignified life. LYN aims to partner with local church to meet these needs through carefully designed interventions impacting communities sustainably.
new w-08

Proclaiming

ማብሰር

ሰው አካላዊ ብቻ ሳይሆን ሥነ-ልቦናዊና መንፈሳዊ ፍጡር ነው። ለመኖር መብል፣ መጠጥ፣ አልባሳትና መጠለያ እንደሚያስፈልጉት ሁሉ ተስፋም ያስፈልገዋል። ያለ መብል፣ መጠጥ፣ አልባሳትና መጠለያ ለተወሰነ ጊዜ መዝለቅ ይችል ይሆናል። ያለ ተስፋ ግን መኖር አስቸጋሪ ነው። ሰው አካላዊ ጉድለቱን ለመቋቋምና አልፎም ለመሄድ የሚያስችለው የተስፋ ጥንካሬው ነው። ተስፋ ነገን በብርሃን የማየት ዐቅም ነው። ከአካላዊ ተግዳሮቶቻቸው የተነሳ የተስፋ ጭላንጭል ማየት የተሳናቸው ሰዎች የተስፋን ብርሃን የሚፈነጥቅላቸው ይፈልጋሉ። ላቭ ዩር ኔበር ከማንም ይልቅ እንዲህ ያሉ ሰዎች በአቅራቢያቸው ባሉ የአጥቢያ ቤተክርስቲያናት አማኞች የተስፋ ብርሃን ሊፈነጥቅላቸው እንደሚገባ ያምናል። ይህም እውን ይሆን ዘንድ የተቻለውን ጥረት ሁሉ ያደርጋል።
Humans are not just physical beings; we are spiritual beings too. In addition to our basic needs, we also need HOPE to thrive. We can live a short-while without our basic physical needs being met, but we can’t live without HOPE. Having HOPE helps us overcome challenges. LYN works with local churches to share real HOPE with its neighbors. We do whatever is necessary to be a beacon of light for communities by proclaiming the gospel of HOPE.
new w-12

Shaping

መቅረፅ

ሰው በገሃዱ ዓለም የሚኖረው በአእምሮው የሚያስበውን ነው። ስለዚህ የሰውን ሕይወት አቅጣጫ ለማስያዝ አእምሮውን መቅረጽ ቀዳሚ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ ነው። ሰዎች ሀብት ንብረት ሞልቶ ተርፏቸው ሌላው ሰው አጠገባቸው በእጦት ሲወድቅ ዐይተው እንዲያልፉ የሚያደርጋቸው የአስተሳሰብ ችግር ነው። በሌላው መልኩ በድህነት የሚማቅቁ ሰዎች በውስጣቸው ያለውን ዕምቅ አቅምና በዙሪያቸው ያለውን መልካም ዕድል ተመልክተው ካሉበት አስከፊ ሁኔታ ለመውጣት እንዳይሠሩ ዕንቅፋት የሚሆነው የአስተሳሰብ ችግር ነው። ላቭ ዩር ኔበር ሰዎች ባላቸው ዐቅም ሁሉ በችግር ያሉትን እንዲረዱ፣ ተረጂዎችም ከተቀባይነት ወጥተው በተራቸው ረጂ ለመሆን እንዲጥሩ በአእምሯቸው ወይም በሃሳብ ዓለማቸው ላይ በትጋት መሠራት እንዳለበት ያምናል። ይህንንም ዕውን ለማድረግ ማህበራዊ መገናኛዎችን፣ መድረኮችን፣ የኅትመት ውጤቶችን፣ ሥልጠናዎችንና ሌሎችም መንገዶችን በመጠቀም በአእምሮ መታደስ ላይ ይሠራል።
Humans live out their thoughts. How we think shapes our response to all things around us. That is why some can live in extreme abundance, but they may not be cognizant of the challenges others are facing around them, and the solutions they can provide. That is why it is important to renew the mind. The same is true for those who are facing extreme challenges; the problems become insurmountable, and they are unable to overcome. LYN aims to influence how we see and respond to these challenges. Utilizing different platforms like digital and print media, trainings, etc. it will work on renewing people’s minds.
icn-07

Advocating

መሞገት

ድሆች ለምን ድሃ ሆኑ? የሚለውን ዕድሜ ጠገብ ጥያቄ “ሰነፍ ስለሆኑ፣ የአርባ ቀን ወይም የሰማኒያ ቀን ዕድላቸው ስለሆነ፣ ርግማን ስላለባቸው … ” በማለት በቀላሉ ልንመልስ እንችል ይሆናል። ነገር ግን ድሆች ድሆች የሚሆኑባቸው፣ ድሆችም በመሆኑ የሚቀጥሉባቸው ምክንያቶች ጥልቅ እና ረቂቅ መሆናቸውን ማስተዋል ይጠይቃል። ሰው በተፈጥሮው ድህነትን አይመርጥም ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች ያለፍላጎቱ ድህነት በጫንቃው ላይ ሊቀመጥ ይችላል። ለዚህም አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ ከሚችሉት ነገሮች መካከል የመልካም አስተዳደር እጦት፣ አድልዎ፣ አሳሪ ሕጎችና ደንቦች፣ ሙስና፣ ግጭቶችና መፈናቀሎች በዋነኝነት ሊጠቀሱ ይችላሉ። ድሆች ድምጽ አላቸው፤ ነገር ግን ድምጻቸው እምብዛም አይሰማም። ድምጻቸው እንዲሰማ፣ ከመሰማትም አልፎ እንዲያስተጋባ በዙሪያቸው ያሉ ብዙሃን አብረዋቸው ሊጮሁ ይገባል።
ላቭ ዩር ኔበር ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ መሆን አምላካዊ ጥሪ መሆኑን ያምናል። ስለዚህም አማኞች በዙሪያቸው ስላሉ ድሆች በየደረጃው ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ድምጻቸውን እንዲያሰሙ፣ ሙስናንና ብልሹ አሠራርን ከራሳቸው ጀምሮ እንዲከላከሉ፣ ለማኅበራዊ ሰላምና ፍትህ በትጋት እንዲሠሩ ያበረታታል፣ የበኩሉንም ድርሻ ይወጣል።

why are the poor, poor? There are some standard responses that we can give to answer this lifelong question. However, there is no simple response. There are many factors which contribute to cause, and the solution is just as complex. No one choses to be poor. However, poor governance, time and chance, complex laws, corruption, conflict, displacement, are front runners is the cause-and-effect category. Disadvantaged communities have a voice, but it is rarely heard. LYN aims to be a voice for these voiceless communities. It will advocate for their rights and hold communities accountable as they exercise their rights and fulfill their responsibilities.

new-12

Empowering

ማሻገር

ድሆችን መርዳት ተገቢ ነው። ነገር ግን በተቃራኒው ድሆች ላይ ልናደርስ የምንችለው ትልቁ ጉዳት ሁልጊዜ መርዳት ነው። የተረጂነትና የጥገኝነት አስተሳሰብ ሰዎች ራሳቸውን ለመለወጥ ጥረት እንዳያደርጉ ትልቁ ዕንቅፋት ነው። ይህንን ዕንቅፋት ከመንገድ አስወግዶ በአስከፊ ድህነት ውስጥ የሚኖሩትን ተረጂዎች ወደ አምራችነትና ወደ ረጂነት ለማሻገር ትምህርቶች፣ ሥልጠናዎች እና የመንቀሳቀሻ ድጋፎች ግዙፍ ድርሻ አላቸው።
ላቭ ዩር ኔበር በየአካባቢው ያሉ በአስከፊ ድህነት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች አቅማቸውን ያገናዘበ ትምህርትና ሥልጠና እንዲያገኙ እንዲሁም ለሥራ መንቀሳቀሻ ድጋፎች እንዲመቻቹላቸው በትጋት ይሠራል።

helping is appropriate; however, creating dependency is the risk. LYN will work with its partners to ensure that the right mindset is coupled with the skillsets to lift people out of extreme poverty. This will be done through trainings, and seed funding programs.